Menu
Super User

Super User

የኢሕአፓ (አንድነት) ስምንተኛው ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (አንድነት)፣ ኢሕአፓ (አንድነት) ከሰኔ ፳፬ እስከ ሰኔ ፳፰ ቀን ፪ ሺህ ፲ ዓ. ም (July 1 - 4, 2018) ድረስ በሰሜን አሜሪካ፣ በዳላስ ከተማ ስምንተኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ አካሂዶ በተሳከ ሁኔታ አጠናቅቋል።

በዚህ ታሪካዊ ጉባዔ ላይ አባላት ከተለያዩ ክፍለዓለማት በውክልና የተገኙበት ሲሆን የአገራችንን ተጨባጭ ሁኔታና የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ በሰፊው ከመረመሩ በኋላ ጉባዔው የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።

•ስምንተኛው ጉባዔ በድርጅቱ አመራር የቀረበውን ዘገባ በጽሞና ካዳመጠና ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ አንዳንድ ግብዓቶችን ጨምሮ ዘገባውን ያለ ምንም ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ተቀብሏል።
•አሁን አገራችን ውስጥ የሚታየውን ሕዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተሰፋና ስጋቱን፣ ከዓለምና አካባቢያዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ስምንተኛው ጉባዔ በሰፊው ከመረመረ በኋላ ድርጅቱ በሰላማዊ መንገድ ለመሠረታዊ ለውጥ ለመታገል ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሷል።
•ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን ውስጥ ሕዝባዊ እምቢተኛነቱ በፈጠረው ጫና የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ሊደገፍና ሊበረታታ እንደሚገባው ጉባዔው አምኖበታል። የለውጥ እንቅስቃሴው ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት አገዛዙ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያደረሰውን ጥቃት በመቃወም ከዳር እስከዳር ገንፎሎ በመነሳት እያሳየ ያለው የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ ኢትዮጵያዊነት እንደገና እንዲያንሰራራ የፈጠረውን መንፈስ የኢሕአፓ (አንድነት) ጉባዔ በሙሉ ልብ የሚደግፍና የሚያበረታታ መሆኑን አስረግጦ፣ ይህ መንፈስ የመጨረሻ ግቡን እንዲመታ በሙሉ አቅሙ ለመሳተፍ ወስኗል።

•በአገራችን ውስጥ ያንሰራሩትን ብሄራዊ የፖለቲካና የማኅበራዊ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትንና ዘላቂ ሰላምን ዕውን ለማድረግ ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያሳትፍ ብሄራዊ ጉባዔ መጥራት ሁኔታው የግድ የሚለው በመሆኑ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን የኢሕአፓ (አንድነት) ጉባዔ ይጠይቃል። ለተግባራዊነቱም የራሱን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

•አገራችን አሁን የይቅርታና የመደመር አየር የሚስተጋባበባት መድረክ ሆናለች። ይህ የመደመር መርህ መሠረት በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች ለአገራቸው ሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ ሲባል ልዩነታቸውን አጥብበው በጋራ መሥራት አለባቸው ብሎ ኢሕአፓ (አንድነት) ያምናል። በዚህ መሠረት ጉባዔው የኅብረት ትግልን አስመልክቶ እስካሁን ድረስ ኢሕአፓ ጥረት ያደረገባቸውንና የተሳተፈባቸውን የኅብረት ትግሎች በሰፊው መርምሯል። ስለሆነም አሁን በመሬት ላይ ያለው ሃቅ በኅብረት መታገል ውጤታማና ተስፋ ሰጭ ስለሆነ ኢሕአፓ (አንድነት) እስካሁን ሲከተለው የነበረውን በኅብረት የመታገል አቋሙን በማደስና በማጠናከር ከኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ጋር በመሆን ከዚህ በፊት ከነበረው በበለጠና ሌሎችንም ሊያሳትፍ በሚችል ጥንካሬ ለዴሞክራሲና ለሀገር ሉዓላዊነት የሚደረገውን ትግል አጠናክሮ ለመቀጠል ጉባዔው ወስኗል።

•ጉባዔው የቀድሞ አባሎችን በሚመለከት ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ከሌላኛው የኢሕአፓ ክፍል ጋር ተነጋግሮ እንደ ድሮው ኢሕአፓን አንድ አድርጎ ለመሥራት ወስኗል። ይህንን የስምንተኛውን ጉባዔ ውሳኔ አስመልክቶ ደብዳቤ በቀጥታ ለኢሕአፓ ለማቅረብ ወስኗል።
•ህወሓት በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና የአምባገነን አገዛዙን ለራሱ በሚያመች መንገድ በሕዝባችን ላይ ለመጫን አቅዶና ሰንቆ ያመጣውን ሕዝብን ከፋፍሎ ለመግዛትና ኢትዮጵያዊነትን የሚያኮስምነውን የፌደራል አወቃቀር ጉባዔው በጥልቀት ከመረመረ በኋላ ይህን አገር

የሚያፈራርስና ሕዝባችን እርስ በእርሱ የሚያፋጅ የአገዛዝ ስልት በሙሉ ድምጽ ውድቅ አድርጓል።

•ከዚህ ጋር በተያያዘ በርካታ የአመራር አባሎቻችን በሜዳና በከተማ በህወሓት ታፍነው ተወስደው ላለፉት 27ና ከዚያም በላይ ዓመታት የት እንደደረሱ አይታወቅም። ስለዚህ መንግሥት ታፍነው የተወሰዱ አባሎቻችንን መዳረሻ እንዲያሳውቀንና በሕይወት ያሉትንም በተሰጠው የምህረት አዋጅ መሠረት ከእስር እንዲለቀቁ ጉባዔው በሙሉ ድምፅ ጠይቋል።

•በድርጅቱ አባላት ተጠንቶ የቀረበውን የፌደራል አወቃቀር በሰፊው መርምሮ መጨመር አለባቸው ብሎ ያመነባቸውን ጠቃሚ ግብዓቶች ጨምሮ ጥናቱን ላቀረበው ኮሚቴ ተሰጥቷል። የመጨረሻውን የተጠናቀቀ ሰነድ በ15 ቀናት ውስጥ ለአባላት እንዲያቀርብ ጉባዔው ለኮሚቴው መመሪያ ሰጥቷል።

•ጉባዔው ቋንቋን በሚመለከት ሰፊ ውይይት አካሂዷል። ብሄረስቦች የአካባቢያቸውን ቋንቋ እንዲጠቀሙ፣ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ የሚለውን የቆየ የድርጅቱን አቋም አሁንም የበለጠ አጠናክሮ አፅድቆታል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ኦሮምኛ በአገራችን ውስጥ በርካታ ሕዝብ የሚናገረው ቋንቋ በመሆኑ፣ ከአማርኛ በተጨማሪ ሁለተኛ የሃገሪቱ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጉባዔው ወስኗል። የመጻፊያ ፊደልን በተመለከተ ከላቲን በተሻለ የግዕዝ ፊደል ኦሮምኛን ይገልጸዋል ብሎ ጉባዔው ስላመነ የግዕዝ ፊደል የኦሮምኛ የመጻፊያ ፊደል እንዲሆን ወስኗል።

•በመጨረሻም ከሰባተኛው ጉባዔ ጀምሮ በማገልገል ላይ የቆዩትን የአመራር አባሎችን አመስግኖ በእነሱ ቦታ አዲስ የድርጅቱን ከፍተኛ አመራር አባላትንና የአባላት መብት አስጠባቂ ኮሚቴን በመምረጥ ጉባዔው ተጠናቋል።

ሐምሌ ፭ ቀን ፪ ሺህ ፲ ዓ. ም July 12, 2018

እንኳን ደስ ያለን!

August 2, 2018

በ PDF ለማንበብ ይህን ይጫኑ 

ሰላም ለሰው ልጅም ሆነ ለፍጥረታት ሁሉ አስፈላጊ ሰላምን ለማግኘት የሚከፈለ ዋጋ በአሃዝ መተመን አይቻልም። ለመድረስ የሚኬደ ንገድ፣ ረዥም፣ አድካሚና ጠመዝማዛ ነው። ሰላምን ለማም ትዕግሥት፣ ጥበብና ከፍተኛ ጽናትንም ይጠይቃል። ሰላም ሲኖር ሰዎች የተረጋጋ ሕይ ይኖራቸዋል ቤተሰብም ጥሩ ሕይወት መምራት ችላ ሀገርም በልማት ጎዳና መጓዝ ችላ

በአንዲት አገር ውስጥ ሰላም ካለ ኅብረተሰቡ ምርት ያመርታል በተለያዩ ዘርፎች አገልግሎቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ርጋል አገርንም ያለማል፣ ሳድጋል። ሰላም ሲኖር በፖለቲካ ይሁን በሃይማኖት ወይም በሌሎ ዳዮ የተነሳ ጥላቻ ከመፈላለግና ከመ ይልቅ ዓላማዎችንም ሆነ ዕምነቶች በመከባበር ማራመ ቻላል። የፖለቲካው አየር ሲደፈርስ ግን የኅብረተሰቡን በአጠቃላይ በተለይም ግሞ የቤተሰብን ሰላማዊ ሕይወት ያውካል። የአ ኤኮኖሚም በዚያ ልክ ይቀጭጫል። ስለሆንም ለቤተሰብ ለማኅበረሰብና ለአገር ግንባታ ተፈላጊ ነው።

በሃራችን ውስጥ ባለፉት 27 ዓመታት ሰላም በማኅብረሰባችን ሰላም በሃይማኖት አባቶችና አማኞች ዘንድ ጠፍቶ፣ ሕዝባችን በአካል በመንፈስና በሕይ ከፍ ያለ ዋጋ ሲከፍል ቆይቷል። ለሰላም ዋና ምክንያት የኢህአዴግ/ህወሓ አገዛዝ ነበር።

ህወሓት ገና ልጣ እንደያዘ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ የሆኑትን ፓትሪያርክ ከቀኖና ቤተክርስትያን ውጭ፣ አገዛዙ ትዕዛዝና ማስገደድ፣ ከአገር አባሮ የሰ ቤት የሆነችው ቤተክርስቲያ በሁለት ተከፍላ ንድትታመስ አደረገ። ዓለም በቃኝ ብለው የተሰደዱ መነኮሳት አገዛዙ ድሬዎች ዳማቸ ተባረሩ፣ ታሰሩ፣ እንዲሁም

ተገደሉ። ለሕዝበ-ክርስቲያኑ ሰላምን የምትሰብከ ቤተክርስቲያን ሰላም ውስጧ ጠፍቶ ለ27 ዓመታት ስትታወክ ረች

የእስልምና ይማኖት ተከታዮችንም መንግሥት ተብዬው ከሁለት በመፈልና በመካከላቸው ከፍተኛ ብጥብጥን በማስነሳት አንዱን ክፍል ወግኖ ሌላውን በተከበረው ስጅድ ውስጥ ወታደሮች አሰማርቶ አማኞችን ጨፈጨፈ። መብታች ይከበር ያሉትን በግፍ እስርቤት ወርውሮ ለዓመታት አሰቃያቸው። ሰላም የሚሰበክባቸው ቤተ-ዕምነቶች አጥተው፣ አገዛዙ መዕምና እርስ በእርስ እንዳይተማመ የካድሬ ሰላዮችን ውስጣቸው ሰግስጎ ሲያፋጃቸው ቆየ።

ይሁን እንጂ ግፍ ያንገፈገፈው የሕዝባችን የትግል ውጤት የሆነው የዶ/ አብይ አመራር ሰላምና ይቅር ባይነት ሀገራች ውስጥ እንዲሰፍን ጥረት በማድረጉ፣ ሆድና ጀርባ የኖሩት ሲኖዶችና ልሶ በመሃላቸው ዕርቀ-ሰላም አውር ምዕመኖቻቸው ሰላማዊ ኑሯቸውን መኖር ጀምረዋል። የኢትጵያን ሕዝብ ሁሉ ያሰደስተና ያስደመመ እርምጃ ው።

ኢሕአፓ (አንድነት) በኢትጵያ ውስጥ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲመጣ ታግሏል፣ ከፍተኛ ዋጋም ክፍሎበታል። ታሪክ ምስክሩ ው፣ ባሰራጫቸው መግለጫዎችና የጥናት ጽሁፎችም በግልጽ የተቀመቸው። በመሆኑም ኢሕአፓ (አንድነት) የተወሰውን የሰ እርምጃ ያደንቃል እንቅስቃሴውንም ሙሉ በሙሉ ይደግፋል እነዚ ሁለት ታላቅና ታሪካዊ የእምነት ቶች ከጾሎት ቤትነታቸው አልፈው ለሀገር ስላምና ፍቅር የሚሰበክባቸው ቦታዎች በመቸው፣ ለሀገሪቱ መሠረቶች ቸው። እንደ ዕምነት ቤትነትም ያለ ምንም የመንግሥት ልቃ ብነት አስተምሯቸውን ንደሚቀጥሉ ኢሕአፓ (አንድነት) ያለውን እምነት በዚ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል። የተጀመረው የአንድነትና የፍቅር ሂደ እንዲያድግና ተጠና እንዲቀጥል፣ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ሁሉ ግፉትና ሊንከባከቡት ይገባል።

ሰላምና ዴሞክራሲ የሀ ዋልታ ነው!

የሱዳን ወታደሮች ድንበራችን ተሻግረው በሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማደረሳቸውን በተመለከተ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

Ethiopian People's Revolutionary Party (EPRP)

(አንድነት/United)

ሰኔ ፳፰ ቀን ሺህ ዓ.

July 6, 2018

ድንበራችን ሲደፈር ያመናል

የሱዳን ወታደሮች ድንበራችን ተሻግረው በሕይትና በንብረት ከፍተኛ ዳት ማደረሳቸውን በተመለከተ

አገራች ኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ፣ በመተማ ወረዳ በኩል ልዩ ስሙ ዳሎል ተብሎ ሚጠራው አካባቢ በሰላማዊ መንገድ በእርሻና በንግድ ሥራ ተሰማርተው በሚኖሩ ኢትጵያያን የሱዳን ወታደሮች ድንበራችን ጓንግ ወንዝን ተሻግረው በሕይትና በንብረት ከፍተኛ ዳት ማድረሳቸውን መስማት የሚያበሳጭ ዜና ው። ነገሩን የበለጠ አሳዛኝ የሚያደርገው ደግሞ ከጎረቤት ጦር ጋር ተመሳስሎ ብቶ በምርኮ የተያዘው የትግራይ ክልል ወታደር ነው የሚለው የበለጠ ያሳምማል።

የሱዳንና የኢትጵያ ድንበር ለረዥም ዘመን የሚታወቀው የተፈጥሮ ድንበር በጓንግ ወንዝ ው። ይህን ድንበር አልፎ መተንኮስና ሰላም ማደፍረስ መዘዙ ለሁለቱ አገሮች የሚበ አይደለም። የሱዳን መንግሥት ይህን የጥፋት ዘመቻ የጀመረው ሆን ብሎ ኢትጵያያን በሀራችንና በነፃነታችን አደጋ ሲደረስ ዝም ብለን የምንመለከተው እንዳል ያው ባል።

እነ ምን ርጉ ከኛ ሰው ሲታጣ” እንደተባለው ከዚ ቀደም ከ60 ኪሎ ሜትር የሆነ የሀገራችንን መሬት ህወሓ/ኢህአዴግ አገዛዝ መሰጠቱ የእግር እሳት እያንገበብን ባለበት ቁስል የሕዝባችንን አጥፍቶ የልማት ቦታዎችን ለመያዝ የተደረገውን ሙከ በዝምታ የምናልፈው አይለም። የሱዳን መንግሥት ወረራ የሚያካሄደው ጥቅማቸው የተነካባቸውን የህወሓት ቱባ ባለሥልችና ባለ ሀብቶች ጠራራ ፀሐይ ያጡትን ልጣ ለማስመለስ አስቦ እሳቱ ራሱ በሱዳን መንግሥት የሚነድበት ሆኑ ሊገነዘበ ባል።

በሰ ሠርተው በሚኖሩበት አገራቸው ነብሰ-ገዳይ ወታደ ልኮ ያለምንም ንያት የሰው ትና ንብረት ያጠፋ የሱዳን መንግሥት ከተጠያቂነት የማያመልጥ ሆኑ ነዘበ ባል። በተለይም አሁኑ ሰዓት የሱዳንና የኢትጵያ ሕዝቦች ንግድ በልዩ ልዩ ግንኙነቶች የጠበቀ በሚባልበት ወቅት እንዲህ ዓይነት ጠብ አጫሪነት ከዚያም ቤት እሳት አለ” የሚለውን ኢትጵያዊ አባባል ከግምት ያስገባ አይመስለንም።

ከጦርነቱ አካባቢ የሚደርሰን ዜና እንደሚያመለክተው፣ የትግራይ ክልል የወታደር አዛዥ በሱዳን የወታደር ልብስ ራሱን ደብቆ ጦሩን ሲመራና ሲዋጋ መማረኩን ስምተናል። ከዚህ በተጨማሪ በሱዳን በኩል ሲዋ የሞቱ የህሓት ወታደሮች አስከሬን ኘቱም ሌላ ረጃ ተብሏል። የህሓት በዚህ በአገር ክህደት በሚያስጠይቅ ወንጀል መሳተፍ እውን በሀ ክህደት ወንጀል ሊጠየቅ ባል። ለዚህ ደግሞ በቦታው ተገኝቶ ሁኔታውን የሚያ ቡድን እንዲላክና ተይዟል የሚባለው ተጠርጣሪ ለኢትጵያ ወታደሮች ተሰጥቷል ስለሚባል ዳዩ በአስቸኳይ ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን ኢሕአፓ (አንድነት) ይጠይቃል።

የአካባቢው ሪና የመከከያ ኃይል ወራሪውን ኃይል መትቶ ወደ በት እንደሚሸኘው አንጠራጠርም። ይሁን እንጂ ድንበር ጥሶ የመግባት ስተት ከዚ በፊትም ተደጋጋሚ የተሞከረ ስለሆነ የኢትጵያ መንግሥት የተጠናከረ ድንበር ጠባቂና የሕዝባችን ደህንነት የሚያረጋግጥ የመከላከያ ኃይል ቋሚነት እንዲመ ኢሕአፓ (አንድነት) ይጠይቃል።

በመጨረሻም በዚ ወራሪ ኃይል ወታቸውን ላጡ ቤተሰቦ መጽናናቱን እንመኛለን። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚጠበቁ ቀጣይ እርምጃዎች

ግንቦት 28 ቀን 2010/June 05, 2018
የአገራችንን ሕዝብ ከሚያስከብሩት ባህሪያት አንዱ የሚያስደንቅ፣ አንዳንዴም እልህ የሚያጨርስ እርጋታው ነው። ይህንንም ገፀ- ባህሪ በዘፈኖቹ፣ ውብና ድንቅ በሆኑ ተረቶቹና አባባሎቹ እየቋጠረ ለትውልድ ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ዶክተር አብይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ ባደረጓቸው ንግግሮችና በወሰዷችው እርምጃዎች የተማረከ፣ በርካታ የአገራችን ሕዝብ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ዓይነት እርጋታ በተላበሰ መልኩ እስቲ እንያቸው የሚል ወደ ድጋፍ ያዘመመ አቋም ይዞ ሰንብቷል። በሌላ በኩል ደግሞ አናሳ ድምፆች አሁን የተያዘውን የለውጥ ሂደት በጥርጣሬ ዓይን የሚመለከቱ ክርክሮች ሲያሰሙ ተደምጧል።
ካለፈው ሣምንት ጀምሮ ከዶክተር አብይ መንግሥት በኩል የሚወርዱ ዜናዎች፣ እስካሁን በቃላት ብቻ ሲገለጽ የሰነበተውን የለውጥ አቅጣጫ በተግባር የሚተረጉሙ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውን ያበስራሉ። ከነዚህ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የተላለፈው ውሳኔ፣ እነ አቶ አንዳርጋቸውን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን መልቀቅ፣ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ከሽብርተኞች ስም ዝርዝር መሰረዝ፣ የሽብርተኛ አዋጅ የተባለውን ድንጋጌ ለማሻሻል የተወሰደው እርምጃ ወዘተ.. ይገኙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የጦር ኃይል መሪዎችን ሰብስበው፣ ጦሩ ብሄራዊና ሙያተኛ ጦር መሆን እንደሚገባው ያስተላለፉት መመሪያ የሚደገፍ ነው። ሸንጎ እስካሁን የተወሰዱትን እርምጃዎች በአዎንታዊ መልክ እንደሚመለከታቸው እየገለጽን ወደፊትም አገሪቱንና ሕዝቡን ወጥረው የያዙ አፋኝ ህጎች በሙሉ እንዲሰረዙ ለሚደረገው ጥረትና ሌሎችም በሀገራችን ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚረዱ፣ የሕዝባችንን ጥቅም የሚያስጠብቁና መብቱን የሚያስከብሩ እርምጃዎች በተወሰዱ ቁጥር በአወንታዊና መልክ እንደምንቀበላቸውና ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሊያሸጋግሩ የሚረዱ እርምጃዎች በመሆናቸው የምንደግፋቸው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
እነዚህ በቅርብ ጊዜ የተወሰዱ እርምጃዎች፤ ተስፋ ሰንቆ ለቆየው ሕዝብ ተጨማሪ መተማመኛና ጉልበት ከመሆናቸውም ባሻገር የተጠራጣሪዎችንም ልብ የሚያረጋጉ ክስተቶች እንደሚሆኑ አያከራክርም። ይህ ሁኔታ በለውጥ ፈላጊው ጎራ ውስጥ ውህደት፣ ስምምነት ብሎም ኃይልና ጥንካሬ የሚፈጥረውን ያህል፣ በለውጥ አጋች ቡድን ውስጥ ደግሞ ፍርሃትና ሽብር እንደሚፈጥርም ሰሞኑን በገሃድ መታየት ጀምሯል። አሁን ባለው መንግሥት ውስጥ በለውጥ ፈላጊዎችና በለውጥ አጋቾች መካከል ትግልና መተናነቅ በግልጽ እየተጋጋመ ነው። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ለማስመሰል የሚደረግ ሽኩቻ ነው በሎ መገመት ትልቅ ስህተት ነው። በዚህ ትግል ውስጥ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሕዝቡ ሚናቸውን መለየት ይኖርባቸዋል። ሕዝቡም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶች ከለውጥ ፈላጊዎች ጋር ተሰልፎ እስካሁን የተገኙትን ድሎች በመጠቀም የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት ሕዝባዊ ትግሉን ማስቀጠል የግድ ነው።፡ በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ በአገዛዙና ከአገዛዙ ውጪ ያለው የለውጥ ፈላጊ ኃይል ተባብሮ የሚገፋ ካልሆነ የለውጡ ሂደት እንዳይጨናገፍ እንሰጋለን።
ከላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የዶክተር አብይ መንግሥት ብሄራዊ መግባባትንና የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ደረጃ እስካሁን ያልተመለሱ ጥያቄዎችን እንዲመልስ አበክረን እንጠይቃለን። ከነዚህም ውስጥ እጅግ አጣዳፊ ናቸው ብለን የምናምንባቸው፦
• ብሄራዊ መግባባትን እውን ለማድረግ፤ በመንግሥትና በተፎካካሪ ኃይሎች መከከል ጉባዔ አድርጎ ዋና ዋና የአገሪቱን ችግሮች ለመፍታት እርምጃ መውሰድ፣
• በውጭ አገር ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገራቸው ውስጥ ገብተው ለመንቀሳቀስ እንዲችሉ የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ህግ ማወጅ፣

• የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በሙሉ በአንድ አዋጅ መልቀቅ፣ መዳረሻቸው የጠፋ እስረኞችን መኖር/መሞት ማሳወቅ፣
• በሲቪክ ድርጅቶችና በነፃ ፕሬስ ላይ የተጫኑ አፋኝ ህጎችን ማንሳት የሚሉት ናቸው።

ዜጎች ሁሉ የተገኙትን ድሎች እየተንከባከቡ፤ ለበለጠ ለውጥ ተግተው ይሠራሉ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ይቀጥላል!

Subscribe to this RSS feed