ሜይ ዴይ - የሠራተኞች ቀን
- font size decrease font size increase font size
በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በየዓመቱ ሜይ ዴይ በመባል የሚታወቀው በሜይ ወር በመጀመሪያው ዕለት (ሚያዝያ 23) የሚከበረው የሠራተኞች ቀን ላብ-አደሮች ያለማሰለስ የሚያደርጉትን ትግል፣ እስካሁን ለኅብረተሰቡ ያበረከቱትን አስተዋጽዖና ወደፊትም የሚጠብቋቸውን ተግባራት ለመዘከር ነው። በዓሉ መከበር የጀመረው በ19ኛው ክፍለ- ዘመን በኢንዱስትሪ ባደጉት በምዕራብ አገሮች ላብ-አደሮች ግምባር ቀደምትነት ሲሆን፣ ዓላማውም ለመሠረታዊ የሠራተኛ መብቶች ተፈጻሚነት ነው። እነዚህም ዝቅተኛ የቤተሰብ ወጭን ሊሸፍን የሚችል ክፍያ ለማግኘትና ለሠራተኛ ጤንነት፣ አካልና ሕይወት ተስማሚ የሥራ ሁኔታ እንዲኖር፣ ትርፋቸውን ብቻ የሚያሳድዱት አሠሪዎች ለሠራተኞቻቸው አግባብ ያለው ክፍያ እንዲያደርጉ ለማስገደድ ነው። ይህ አመፃቸው በብዙ አገሮች የሚያረካ ባይሆንም ተፈጻሚነት ግን አግኝቷል።......ቀሪውን አስነብበኝ