Menu

አትረፍ ያለው በሬ ቆዳው ነጋሪት ይሆናል

 


ሰሞኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃንና በራሱ በህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ እንደተረጋገጠው፣ በደቡብ ሱዳን በኩል ድንበር ጥሰው የመጡ ታጣቂዎች በጋምቤላ አካባቢ በሚኖረው ሕዝብችን ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ ፈጽመዋል። ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት ስንሰማ የተሰማን ኃዘን መሪር ነው። ኢሕአፓ (አንድነት) ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖቻችን መጽናናቱን እንዲሰጥልን ይመኛል።

የጋምቤላ አካባቢ ሕዝብ ህወሓት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በአገዛዙ ታጣቂዎች ሲቀጠቀጥና በልማት ስም መሬቱን በውጭ ባለሀብቶችና በህወሓት ባለሥልጣናት በመነጠቁ፣ ልጆቹንና ከብቶቹን ይዞ ቀየውን ለቆ ወደ በረሃ በመሰደድ እየተንገላታ ያለ ሕዝብ ነው። መሬታችንን ለቅቀን አንሄድም ብለው የተከራከሩ ገበሬዎችም በአገዛዙ ታጣቂ ኃይሎች የቁም ስቃይ እያዩ ሕይወታቸውን አጥተዋል። አሁንም ለሕዝብና ለሀገር ሉዓላዊነት ደንታ የለሹ መንግሥት ተብየው ጋምቤላ በፌደራል ሥር መሆን አለባት በማለት የአካባቢውን ሚሊሺይ በትኖ ደንበሩን ያለጠባቂ በማስቀረቱ፤ የጎረቤት አገር ታጣቂዎች ድንበራችንን ጥሰው በመግባት ከሁለት መቶ በላይ ወገኖቻችንን ሲገድሉ፣ በመቶ የሚቆጠሩትን አቁስለው በርካታ ሕፃናትንም አፍነው ወስደዋል። በህወሓት/ኢህአዴግ ዘገባ 2000 የቀንድ ከብቶችም እንደተወሰዱ ተነግሯል። የወጣለት መደፈር፣ የነጠረለት ብሔራዊ ውርደት ይሏል ይህ ነው። .......ቀሪውን አስነብበኝ

back to top