Menu

አገራችንንና ሕዝባችንን የሚጎዳ ስምምነትን ሁሉ እናወግዛለን!

የኢትዮጵያን የደም ሥር ዓባይን በተመለከተ አንዳንድ መሠረታዊ ጉዳዮችን ለማስጨበጥ እንወዳለን። እነዚህንም በአራት ክፍሎች ለይተን እናቀርባለን።

1) ታሪካዊ ዕውነታዎች፦ አሁን የያዝነው 21ኛው ክፍለ-ዘመን ዓለም በውኃ እጥረት ምክንያት ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ላይ የወደቀችበት ጊዜ ነው። ለዚህ የውኃ እጥረት በርካታ ዋና ዋና ምክንያቶች ቢኖሩም፣ የሚከተሉትን ሁለት ዓብይ ጉዳዮች ለአብነት ያህል እንጠቅሳለን።

) የአየር ንብረት መዛባት፦ የአየር ንብረት መዛባት የዝናብ እጥረትን በማስከተሉ የትልልቅ ወንዞች ውኃ እየቀነስ መምጣቱን የአየር ንብረት ጠበብቶች ይናገራሉ። እንዲሁም ውኃ ከከርሰ ምድር እያወጡ የሚጠቀሙ አገሮች በዓለም ዙሪያ እየደረሰ ባለው የዝናብ እጥረት ምክንያት የውኃ እጥረትም የሕይወት ከፍተኛ ጥያቄ ሆኗል።

) የሕዝብ ብዛት መጨመር፦ በዓለማችን የሕዝብ ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የየአገሮችን የውኃ ፍላጎት በእጅጉ ከፍ እንዲል አድርጎታል። ስለሆነም የተፈጥሮ ውኃ ባለፀጋ የሆኑ አገሮች በከፍተኛ ደረጃ የፀጥታ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን እየተገነዝብን ነው። ኢትዮጵያም በዓባይ ምክንያት ከዚህ ቀደም ተኝተውላት የማያውቁት ጠላቶቿ ሁሉ አሁንም ስለማይተኙላት ለፀጥታዋና ለህልውናዋ አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች ሁሉ እየተባባሱ ስለሚመጡ ኢትዮጵያውያን ሁኔታውን ትኩረት ልንሰጠው

ይገባል። የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ይሁን እንጂ በመልካም አስተዳደር እጦትና በብቃት ጉድለት ምክንያቶች ባላት የውኃ ሀብት ላይ መብቷን ተጠቅማ ወንዞቿን ለአገር ዕድገትና ልማት ለማዋል አልቻለችም።   አገራችን ከኤኮኖሚና ከሰው ኃይል ጥንካሬ በተጨማሪ ለሕዝብ መብትና ለሀገር ጥቅም የቆመ መንግሥት ብታገኝ፣ የውኃ ሃብቷን በሕጋዊ መንገድ የመጠቀምና የባለቤትነት መብት ሊነፈጋት ባልተገባ ነበር። በዓባይ ውኃ ምክንያት አገራችን ለብዙ ዘመናት አያሌ ጠላቶችን አፍርታለች። እነዚሁ ጠላቶቻችንም አገራችንን ለማዳከምና ለመበታተን ብዙ ጥረቶችን ሲያደርጉ ኖረዋል፤ አሁንም እያደረጉ ነው። ከእነዚህ አገሮች አንዷ የሆነችው ግብፅ በአገራችን በሰሜኑ፣ በምሥራቁና በምዕራቡ ክፍሎች በተለያዩ ጊዜያት በቀጥታ ጦርነት ከፍታ ለሽንፈት ተዳርጋለች። ይህ በአገራችን ላይ ያደረገችው ቀጥታ ወረራ ቢከሽፍባትም፣ በዓለም መድረክ ላይ የዓባይ ሙሉ ተጠቃሚና ባለቤት ግብፅ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለችም በማለት ከፍተኛ ድጋፍ እንድታገኝ ያላሰለሰ ጥረት በማድረጓ ብዙ ደጋፊዎችን አፍርታለች። ,,,,,,, ሙሉውን አስነብበኝ

back to top