የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከውድቀት አያድንም!
- font size decrease font size increase font size
የህወሓት አገዛዝ ከተወጠረበት ሁኔታ ለመውጫ ይጠቅመኛል ብሎ ስላሰበ፣ አንቀጽ 93ትን ተጠቅሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። በትክክል የአዋጁ ዓቢይ ዓላማ ግን የመንግሥትን ኢ-ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ በመቃወም የተቀጣጠለውን የሕዝብ አመጽ ለማጨናገፍ፣ ለማኮላሸትና ከተቻለውም ጨርሶ ለማዳፈን ነው። በዚህ ድርጊቱም ህወሓት ከዚህ በፊት ከገደለው የበለጠ ብዙ ሕዝብ ሊጨርስ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፣ ዋና ዓላማው ሕዝብን ረግጦ፣ አፍኖና ጨፍጭፎ በሥልጣን ላይ መቆየት ነውና። ዓላማው ይህ መሆኑ በግልጽ እየታወቀ፣ የመገናኛ ሚኒስተር ተብዬው ግን ሲያድበሰብስ አዋጁ የታወጀው በሕዝቡ አመጽና ሰልፍ ምክንያት አይደለም ይለናል። ይህን “ተጨፈኑ ላሞኛችሁ” አባባሉን አንድ ጣቱን የሚጠባ ልጅንም እንኳን ሊያታልል አይችልም። .....ሙሉውን አስነብበኝ
Last modified onFriday, 14 October 2016 10:29