| Party Program Amharic |
|
“…የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 6 ቀን 1998 ዓ. ም. አራተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ ይህንን የፖለቲካ ፕሮግራም እንደገና በማሻሻል አፅድቆ አውጥቷል። ይህ ፕሮግራም የኢሕአፓን አቋሞችና መሰረታዊ ዓላማዎች የሚያንፀባርቅ ነው። ኢሕአፓ ከተመሰረተበት ከሚያዝያ 1964 ዓ. ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነፃና ርትዓዊ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መንግስትን እንዲመሰርትና መብቱም ተከብሮ ሉዓላዊነትዋ የተጠበቀች ሃገሩን በሁሉም መስክ ለመገንባት እንዲችል ታግሏል። ኢሕአፓ ሶስት ልዩ ልዩ አገዛዞችን ከሕዝብ ጎን ሆኖ የታገለው እነዚህ አገዛዞች የሕዝብን መብት ረግጠው ጨቋኝ ስርዓቶችን ስለመሰረቱና መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣትም ዝግጁነት የሌላቸው ሆነው በመገኘታቸው ነው። መሬት ለአራሹ፣ ዴሞክራሲ ለጭቁኑ ሕዝብ፣ የሀገር ሉዓላዊነት ይከበር፣ አንድነት በዴሞክራሲና በእኩልነት መሰረት ላይ ይረጋገጥ፣ ፍትሕና የሕግ የበላይነት ይስፈን ወዘተ እያለ ኢሕአፓ ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍሎ ለሕዝብ የገባውን ቃል ኪዳን በማክበር ታግሏል። በዚህም ረጅም የትግል ሂደት ድርጅቱ በትግል ከትግል እየተማረ፤ ከስህተቱ ተምሮና ታርሞ ጠንካራ ጎኑን በይበልጥ አጠናክሮ፤ ተጨባጩን ሁኔታ በማጤን ፕሮግራሙን እያሻሻለና እያስተካከለ በጽናት ቀጥሏል። አራተኛ ጉባዔውም ዛሬ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በመመርመር እስከዛሬ ይሰራበት በነበረው የፖለቲካ ፕሮግራም ላይ አስፈላጊውን ማሻሻያ አድርጎ እነሆ አቅርቧል። …”
ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ድርጅቱን ይበልጥ ለማጠናከርና ወደፊት ለማስቀጠል የገባውን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ወደፊት የሚፈጠሩ ብሔራዊና ዓለማቀፋዊ ፖለቲካዊ አስገዳጅ ሁኔታዎች እስኪከሰቱ ድረስ በአራተኛው የአባላት አጠቃላይ ጉባዔ ላይ የጸደቀውን የፖለቲካ ፕሮግራም ይቀበላል፤ ለተግባራዊነቱም በትጋት ይሰራል። |
| ኢትዮጵያችን |
| ለወቅታዊ አንገብጋቢና መሰረታዊ ችግራችን፣ ዘላቂ አፋጣኝና |
| መሐሉ ዳር ሳይሆን |
| ምርጫና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ |
| ፍትሕ እኩልነትና ዴሞክራሲን ለተጠማ ሕዝብ - ጦርነት? |